Fana: At a Speed of Life!

የኢንተርኔት አባት ለዓለም አቀፉ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ ኢትዮጵያን ያደረገችውን ዝግጅት አደነቁ

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንተርኔት አባት በመባል የሚታወቁት ቪንት ሰርፍ ለዓለም አቀፉ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ ኢትዮጵያ ያደረገችውን ዝግጅት አደነቁ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ እና ቪንት ሰርፍ (የኢንተርኔት አባት) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የኢንተርኔት አባት ለ17ኛው ዓለም አቀፉ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ ኢትዮጵያ ያደረገችውን ዝግጅት አድንቀዋል፡፡

በጉባዔው ላይም የኢትዮጵያውያንን ጥሩ እንግዳ ተቀባይነት ማየታቸውን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ጉባዔውን በማዘጋጀት በበይነ መረብ አስተዳዳር ላይ ያላትን ቁርጠኝነት አሳይታለች ብለዋል ሰርፍ፡፡

ዶክተር በለጠ ሞላ በበኩላቸው÷ ቪንት ሰርፍ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በጉባዔው በመሳተፋቸው እና ለዓለም አቀፉ የበይነመረብ አስተዳደር ጉባዔ ልምዳቸውን በማካፈላቸው አመስግነዋል።

በቀጣይም አብሮ መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.