የሀገር ውስጥ ዜና

ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች በድሬዳዋ ከተማ እየተከበረ ነው

By Alemayehu Geremew

December 03, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች በድሬዳዋ ከተማ እየተከበረ ነው ።

እለቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ በሃገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ30 ኛጊዜ “አካታች የፈጠራ የሰራና ሽግግራዊ መፍትሔ ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተደራሽነት ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው።

በበዓሉ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰን፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርጎጌ ተስፋየን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በተያያዘም የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በድሬዳዋ ከተማ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።

ሚኒስትሯ የድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታልን ፣ በኢትዮ-ፈረንሳይ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከልን አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል እየተገነባ ያለውን የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጫ ማዕከልን፣ በሆስፒታሉ የህሙማን ቅብብሎሽ ስርዓቱን ለማዘመን የሚረዳውን የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት እና ሥራ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኘውን የሱስ ማገገሚያ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

ሚኒስትሯ የጤና ተቋማቱን አመራሮችና ባለሙያዎችን በማበረታታት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ