የሀገር ውስጥ ዜና

አየር መንገዱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ 80 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሲያደርግ የነበረውን በረራ አቋረጠ

By Tibebu Kebede

March 29, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ 80 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሲያደርግ የነበረውን በረራ ከዛሬ ጀምሮ ማቋረጡን አስታወቀ።

አየር መንገዱ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ የካርጎ( የእቃ ማመላለሻ) በራሮች ግን ይቀጥላሉ ብሏል።