የሀገር ውስጥ ዜና

በሶማሌ ክልል የሙስና መከላከል ኮሚቴ ተቋቋመ

By Shambel Mihret

December 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ አምስት አባላት ያሉት የሙስና መከላከል ኮሚቴ አቋቋሙ፡፡

የኮሚቴው ኃላፊነት  በክልሉ በሙስና ተግባራት ላይ ክትትልና ምርመራ  ማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተደረገው ክትትልና ምርመራ መሰረትም ተሳታፊ ሆነው በተገኙ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ  ኮሚቴው ይሠራል ሲል የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡