ስፓርት

ኔዘርላንድስ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች

By Shambel Mihret

December 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኔዘርላንድስ አሜሪካን 3 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች፡፡

ምሽቱን ኔዘርላንድስ እና አሜሪካ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያውን የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አካሂደዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ሜምፊስ ዴፓይ በ10ኛው፣ዳሊ ብሊንድ በ46ኛው እና ዴንዝል ዴምፍሪስ በ81ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ኔዘርላንድስ አሜሪካን 3 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡

የአሜሪካን ብቸኛ ጎል ደግሞ ሃጂ ራይት በ76ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

የ22ኛው የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት አራት ሰዓት ላይ አርጀንቲና ከአውስትራሊያ ይፋለማሉ፡፡