ስፓርት

አርጀንቲና አውስትራሊያን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

By Mekoya Hailemariam

December 04, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) -አርጀንቲና አውስትራሊያን በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀለች።

ምሽት አራት ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ አርጀንቲና አውስትራሊያን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።

ለአርጀንቲና ጎሎቹን ሌዮኔል ሜሲ በ35ኛው እንዲሁም ጁሊያን አለቫሬዝ በ57ኛው ደቂቃዎች ላይ አስቆጥረዋል።

የአውስትራሊያን ብቸኛ ጎል በ77ኛው ደቂቃ ላይ የአርጀንቲናው ኤንዞ ፈርናንዴዝ በራሱ ጎል ላይ አስቆጥሯል።

ቀደም ብሎ 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ኔዘርላንድስ አሜሪካን 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀሏ ይታወሳል።

በቀጣይ አርጀንቲና ኔዘርላንድስን የምትገጥም ይሆናል።