የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም አቀፉ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት ማጠቃለያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

December 04, 2022

 

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት አከባበር በኢትዮጵያ ማጠቃለያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመርሃ ግብሩ ሚኒስትሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን፥ ሳምንቱ ስኬታማ እንደነበር መግለፃቸውን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ለስራ ፈጣሪዎች አስቸጋሪ የሆኑ አሰራሮች እና ዕድሎች ላይ ውይይት እንደሚደረግ፣ በሳምንቱ በተከናወኑ ውድድሮች ላይ አሸናፊ ለሆኑት ዕውቅና እንደሚሰጥና ከሕዳር እስከ ሕዳር የሚከናወኑ ተግባራት ይፋ እንደሚሆንም አቶ ንጉሱ አመላክተዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ፥ በየዓመቱ ሕዳር ወር ላይ የሚስተናገደው ዓለም አቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት ለሚሊየን ችግሮች ሚሊየን ዕድሎች መኖራቸውን የሚያመላክቱ መርሃ ግብሮች የተከናወኑበት ሆኗል ብለዋል።