የሀገር ውስጥ ዜና

የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በክልል ደረጃ በቁሊቶ ከተማ እየተከበረ ነው

By Feven Bishaw

December 04, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)17ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል በደቡብ ክልል ደረጃ በሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ እየተከበረ ይገኛል ፡፡

በበዓሉ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የኦሮሚያ፣ የአፋር ፣የሲዳማና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በርካታ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ለማ ገዙሜ÷ወንድማማችነትና አብሮነታችን ሁሌም አብረውን የሚቀጥሉ ናቸው ብለዋል፡፡

ድንቅ እሴቶችን ማጎልበትና አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡

መርሃ ግብሩ በባህላዊ ትዕይንቶች የታጀበ ሲሆን÷ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረጋልም ነው የተባለው፡፡

17ኛው የብሄር በሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ የፊታችን ሀሙስ ህዳር 29 ቀን 2015ዓ.ም በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ይከበራል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው