Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ የአውሮፓ ህብረት ያወጣውን የነዳጅ ዋጋ ተመን እንደማትቀበል አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ያወጡትን የነዳጅ ዋጋ ተመን እንደማትቀበል አስታውቃለች፡፡

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ሩሲያ የነዳጅ ምርቷን በበርሜል 60 የአሜሪካ ዶላር እንድትሸጥ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረትም የህብረቱ አባል ሀገራት ከሩሲያ ነዳጅ በበርሜል ከ60 የአሜሪካ ዶላር በላይ እንዳይገዙ እገዳ ተጥሏል፡፡

በተመሳሳይ የቡድን ሰባት አባል ሀገራት እና አውስትራሊያ ከሩሲያ ነዳጅ ከተጠቀሰው ዋጋ በላይ እንደማይገዙ አስታውቀዋል፡፡

የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ÷ሩሲያ የአውሮፓ ህብረትም ሆነ የቡድን ሰባት አባል ሀገራት በነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ ያወጡትን ተመን አትቀበልም ብለዋል፡፡

በአውሮፓ ህብረት ያወጣው የዋጋ ማሻሻያ በሞስኮ ላይ ችግር እንዳያስከትል የተለያዩ አዋጭ መፍትሔዎች ላይ እየተሰራ እንደሆነ መግለጻቸውንም አር ቲ ዘግቧል፡፡

በአንጻሩ ሩሲያ የነዳጅ ገበያውን በተመለከተ ወቅታዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ለመግዛት ከሚስማሙ ሀገራት ጋር በቅንጅት እንደምትሰራ ነው የተናገሩት፡፡

ሀገራት በሩሲያ ነዳጅ ዋጋ ላይ ያወጡት የዋጋ ተመን ዓለም አቀፍ ገበያውን እንደሚያውከው የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የሀገራቱ አካሄድ ዓለም አቀፉን የንግድ ሕግ እንደሚጻረርም አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.