ብራዚል ደቡብ ኮሪያን 4 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ብራዚል እና ደቡብ ኮሪያ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡
በዚህም የአምስት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኗ ብራዚል ደቡብ ኮሪያን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡
የብራዚልን የማሸነፊ ግቦች ቪኒሺየስ ጁኒየር፣ ኔይማር ጁኒየር፣ሪቻርሊሰን እና ሉካስ ፓኪዮታ በ7ኛው፣ በ13ኛው፣በ29ኛው እና በ36ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል፡፡
የደቡብ ኮሪያን ብቸኛ ግብ ደግሞ ፓይክ ሰንግ 76ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
ቀደም ሲል በተደረገ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ክሮሺያ ጃፓንን በመለያ ምት 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀሏ ይታወሳል፡፡
በቀጣይ ለሚካሄደው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታም ብራዚል ክሮሺያን የምትገጥም ይሆናል፡፡