የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የግብርና ምርቶች ለዕይታ የቀረቡበት ዐውደ ርዕይ ተከፈተ

By Shambel Mihret

December 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ግብርናን ትልቅ ተጽዕኖ እንዲፈጥር ማስቻል” በሚል መሪ ሐሳብ የግብርና ምርቶች ለዕይታ የቀረቡበት ዐውደ ርዕይ ዛሬ በአዲስ አበበባ አፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተከፍቷል።

ዐውደ ርዕዩን ያዘጋጁት÷ የግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ናቸው፡፡

በዐውደ ርዕዩ ላይ በግብርናው ዘርፍ የሚሠሩ ማኅበራት፣ የገበሬ ኅብረት ሥራ ማኅበራት እና በግሉ ዘርፍ ያሉ ተቋማት ምርት እና አገልግሎታቸውንያቀርባሉ፡፡