Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የሱዳን ወታደራዊና ሲቭል ሃይሎች የተፈራረሙትን ስምምነት እንደምትደግፍ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት የሱዳን ወታደራዊ እና ሲቭል ፖለቲካ ሃይሎች የተፈራረሙትን የፖለቲካ ማዕቀፍ ስምምነት አድንቋል፡፡
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ÷ሁለቱ ወገኖች የተፈራረሙት ስምምነት ሀገሪቱን ወደ ነጻ እና ተዓማኒ ምርጫ የሚያመራ አዲስ የሲቪል የሽግግር መንግስት ለመመስራት እንደሚያስችል አውስቷል፡፡
 
ኢትዮጵያ የሱዳን ወታደራዊ እና ሲቭል ሃይሎች የተፈራረሙትን ስምምነት ታደንቃለች ያለው ሚኒስቴሩ ÷ ለተግባራዊነቱም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጧል፡፡
 
የኢትዮጵያ መንግስት የሱዳን ወታደራዊ እና ሲቭል ሃይሎች የራሳቸውን እውቀት እና አቅም በመጠቀም የሀገሪቱን ሕዝቦች ፍላጎት እና ተጠቃሚነት ባገናዘበ መልኩ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደሚያሸጋግሩ ሙሉ እምነት እንዳለው ገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.