ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ ተጋጣሚውን ረታ

By ዮሐንስ ደርበው

December 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲን 3 ለ0 አሸነፈ፡፡

የአዳማ ከተማን የማሸነፊያ ጎሎች አቡበከር ወንድሙ በ14ኛው እና አሜ መሐመድ በ72ኛውና በ73ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡

በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም እየተካሔደ የሚገኘው የ11ኛ ሣምንት ጨዋታ መርሐ ግብር ሲቀጥል÷ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ባሕርዳር ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ይገናኛሉ፡፡