የሀገር ውስጥ ዜና

በአለታ ወንዶ ከተማ በአንዲት ግለሰብ መኖሪያ ቤት በርካታ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ

By Amele Demsew

December 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ሀለታ ወንዶ ከተማ በአንዲት ግለሰብ መኖሪያ ቤት በርካታ ህገወጥ የጦር መሳሪያ መያዙ ተገለፀ፡፡ ከብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልግሎት ኦፊሰሮች በደረሰ መረጃ በሲዳማ ክልል ልዪ ኃይል ፖሊስ ክትትል ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸው ተገልጿል፡፡ በዚህም በክልሉ አለታ ወንዶ ከተማ በምትኖረው ወይዘሪት ትዕግስት አበበ በተባለች መኖሪያ ቤት ውስጥ ዛሬ ከምሽቱ 12 ሰዓት የክልሉ ፖሊስ አባላት በአንድ ህገወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ወኪል ተደብቀዉና ተከማችተዉ የተገኙ 97 ሽጉጦች እና 15 የሸጉጥ ጥይቶችን ይዘዋል፡፡