የሀገር ውስጥ ዜና

በሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብዱልከድር የተመራ ልዑክ ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገባ

By Shambel Mihret

December 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብዱልከድር መሃመድ ኑር የተመራ የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የሥራ ስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብቷል።

ለልዑካን ቡድኑ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ይልማ መኳንንቴ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ቡድኑ ለሶስት ቀናት በሚያደርገው የስራ ጉብኝት ከመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች  ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር  በቀጣናዊ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርግ ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡