ስፓርት

ኤደን ሀዛርድ ከቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ራሱን አገለለ

By Mikias Ayele

December 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሁን በሪያል ማድሪድ እየተጫወተ የሚገኘው ኤደን ሀዛርድ ከቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን ይፋ አድርጓል፡፡

ቤልጂየም በጊዜ ከዓለም ዋንጫው መሰናበቷን ተከትሎ ነው ኤደን ሀዛርድ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ያገለለው፡፡

የ31 ዓመቱ ሀዛርድ ለሀገሩ በ126 ጨዋታዎች ተሰልፎ 33 ጎሎችን ማስቆጠሩን ጎል ዶት ኮም ዘግቧል፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ቀደም ሲል ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡