የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል ሰባት አባላት ያሉት የጸረ ሙስና ኮሚቴ አቋቋመ

By ዮሐንስ ደርበው

December 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ሰባት አባላት ያሉት የጸረ ሙስና ኮሚቴ አቋቋመ፡፡

 በኦሮሚያ ክልል ሌብነትን እና ብልሹ አሠራርን ለመታገል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር  ሺመልስ አብዲሳ ሰባት አባላት ያሉት የፀረ ሙስና ኮሚቴ  አቋቁመዋል።

በዚህም መሠረት÷ ኮሚሽነር ጀነራል ከፍያለው ተፈራ ሰብሳቢ እንዲሁም አቶ ጉዮ ዋሪዮ፣ አቶ ተፈሪ ወንዲፍራው፣ ወ/ሮ ኮኮቤ ዲዳ፣ አቶ አብደላ ኦጋቴ፣ ወ/ሮ መሠረት አሰፋ እና ምክትል ኮሚሽነር ዘሪሁን ዱጉማ ደግሞ የፀረ ሙስና ኮሚቴ አባል ሆነው እንዲሠሩ ተሰይመዋል፡፡

የኮሚቴው ሥራ የተሳካ እንዲሆን ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እና ድጋፍ እንዲያደርግ ርዕሰ መስተዳድር ሺመልስ አብዲሳ ጥሪ አቅርበዋል፡፡