የሀገር ውስጥ ዜና

የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ሕብረት ጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሥራ ጉብኝት አደረጉ

By ዮሐንስ ደርበው

December 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ24ኛው የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ሕብረት ጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ከ14 የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የተውጣጣው ልዑክ አባላት ÷ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ በመገኘት በዲጂታላይዜሽን የተከናወኑ የምርመራ ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ለጎብኝዎቹ አቀባበል አድርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባለፉት አራት ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችም ለልዑኩ ገለጻ ተደርጓል፡፡

ጎብኝዎቹ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተከናወኑ ሥራዎችን በተሞክሮነት ወደ ሀገራቸው በመውሰድ በቀጣናው ወጥ የሆነ የፖሊስ ተቋም እንዲገነባ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

በጉብኝቱ ሚኒስትሮች፣ የኢንተርፖል ኃላፊዎች፣ የኬኒያ፣ የሱዳን፣ የደቡብ ሱዳን፣ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ፣ የሲሸልስ፣ የሩዋንዳ፣ የኤርትራ፣ የኡጋንዳ፣ የታንዛኒያ፣ የኮሞሮስ፣ የቡሩንዲ ፖሊስ አዛዦች እንዲሁም ዲፕሎማቶች እና ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡