የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይና የደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይና የኅብረቱ ኮሚሽን ም/ፕሬዚደንት ጆሴፍ ቦሬል ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

March 31, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይና የደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይና የኅብረቱ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚደንት ጆሴፍ ቦሬል ጋር በስልክ ተወያዩ።

በውይይታቸውም አፍሪካ እና አውሮፓ በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ19) ምክንያት የተጋፈጡትን የጋራ ፈተና አስመልክቶ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ አስታውቀዋል።