የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

By Feven Bishaw

December 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

በአፍሪካ ህብረት 24ኛው የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባኤው የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብሄራዊ ፖሊስ ዋና ኢንስፔክተር ጀነራል ዲዩዶኔ አሙሊ ባሂግዋ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ፕሬዚዳንትነታቸውን አስረክበዋል፡፡