ዶ/ር አብርሃም በላይ ከሶማሊያ የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Shambel Mihret

December 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ በሶማሊያ የመከላከያ ሚኒስትር አብዱልከድር መሐመድ ኑር ከተመራው ልዑካ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለትዮሽ የሰላምና የደኅንነት ጉዳዮች እንዲሁም በቀጣናው የፀጥታ ሁኔታ መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ሰላምና ደኅንነት ሁለንተናዊ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል ዶክተር አብርሃም መናገራቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

አብዱልከድር መሐመድ ኑር በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሶማሊያ ሰላምና ፀጥታ መረጋገጥ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት በመክፈል እያደረገው ላለው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

ድጋፉ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችልም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡