Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከአልጄሪያ የውጭጉዳይ ሚኒስትር ራምታን ላማምራ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታን ላማምራ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ኢትዮጵያና አልጄሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

አምስተኛውን የጋራ የሚንስትሮች ጉባዔ ኢትዮጵያ በመጪው መጋቢት ወር እንደምታስተናግድ የተገለጸ ሲሆን÷ ለስኬቱ ከወዲሁ አስፈላጊው ዝግጅት መጀመሩን አምባሳደር ብርቱካን መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ራምታን ላማምራ በበኩላቸው÷ አልጄሪያና ኢትዮጵያ ያላቸውን ጠንካራ ግንኙነት ወደ ላቀ የኢኮኖሚ ትብብር ለማሸጋገር ሀገራቱ ለጋራ የሚኒስትሮች ጉባዔ ስኬታማነት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።

አምባሳደር ብርቱካን አልጄሪያ በአፍሪካ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆነው በሚያገለግሉ ሀገራት መካከል የተሻለ ቅንጅት እንዲፈጠር ለምታደርገው አስተዋፅኦ አመስግነዋል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.