ስፓርት

ኢትዮጵያ መድን እና ሀዲያ ሆሳዕና ድል ቀናቸው

By ዮሐንስ ደርበው

December 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተካሔዱ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ መድን እና ሀዲያ ሆሳዕና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፍዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ሀዲያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡናን ዳግም ንጉሴ በ33ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል አሸንፏል፡፡

በሌላ የ11ኛ ሣምንት የጨዋታ መርሐ ግብር ደግሞ ኢትዮጵያ መድን ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ መድንን ጎሎች ሀቢብ ከማል በ44ኛው እና ያሬድ ዳርዛ በ89ኛው እንዲሁም የወልቂጤ ከተማን ብቸኛ ጎል ጌታነህ ከበደ በ75ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡