የሀገር ውስጥ ዜና

አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ተለያየ

By Mikias Ayele

December 09, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ከኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር በይፋ ተለያይቷል፡፡

አሰልጣኝ ተመስገን ቡድኑን ውጤታማ ለማደረግ ክለቡን ቢረከብም ያሰመዘገበው ውጤት በዝውውሩ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉትን የኢትዮጵያ ቡና አመራሮችን ያስደሰተ አለመሆኑን ተከትሎ ነው ከክለቡ ጋር የተለያየው፡፡

ክለቡ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ባደረጋቸው 10 ጨዋታዎች በአራቱ አሸንፎ በተመሳሳይ በአራቱ ተሸንፎ ሁለት ጨዋታ ብቻ አቻ በመውጣት በሊጉ 14 ነጥብ በመያዝ 9ኛ ደረጃላይ ተቀምጧል፡፡

የክለቡ አመራሮቹ በቀጣዩ 11 ቀን አዲሱን አሰልጣኝ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን÷ለዚህም የውጪ ሀገር አሰልጣኝና የሀገር ውስጥ አሰልጣኞችን በማነጋገር ላይ መሆናቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡