የሀገር ውስጥ ዜና

ከሳዑዲ ዓረቢያ 592 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Melaku Gedif

December 09, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 592 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች መሆናቸውን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉም ተገልጿል፡፡

ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራም 9 ሺህ 660 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡