የሀገር ውስጥ ዜና

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመራ ገቡ

By Mikias Ayele

December 09, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ኤርትራ አስመራ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ የኤርትራ አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ  ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ነው ለስራ ጉብኝት ኤርትራ የገቡት፡፡

ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ እና ልዑካቸው አስመራ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለሁለት ቀናት በአስመራ የስራ ጉብኝት የሚያደርጉ መሆኑንም የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል አስታውቀዋል፡፡