የሀገር ውስጥ ዜና

በተለያየ ጊዜ የተሰረቁ ከ200 በላይ የተሽከርካሪ ስፖኪዮዎች ጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው ተገኙ

By ዮሐንስ ደርበው

December 10, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተለያየ ጊዜ የተሰረቁ ከ200 በላይ የተሽከርካሪ ስፖኪዮዎች ጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን ፖሊስ ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እንዳስታወቀው÷ ስፖኪዮዎቹን እየተቀበሉ በማከማቸት የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው፡፡

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አሜሪካን ግቢ አካባቢ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ግለሰቦቹ በአካባቢው ከላስቲክ በተሠራ ቤት ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ የመኪና ስፖኪዮዎችን አከማችተው መገኘታውን ፖሊስ ገልጿል፡፡

ባለንብረቶች አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል ማስረጃቸውን በማቅረብ ንብረታቸው ስለመኖሩ አረጋግጠው መውሰድ እንደሚችሉ ተመላክቷል፡፡