Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል 98 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የሰብዓዊ እርዳታ መሰራጨቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ከ98 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የሰብዓዊ እርዳታ መሰራጨቱን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በትግራይ ክልልድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚከናወነውያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ተጠናክሮ መቀጠሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም በትግራይ ክልል ምግብ እና አልሚ ምግብን ጨምሮ 89 ሺህ 217 ሜትሪክ ቶን በላይ የሰብዓዊ እርዳታ መሰራጨቱን ተናግረዋል፡፡
 
ከዚህ ውስጥም 13 ሺህ 686 ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆነው በኢትዮጵያ መንግስት የተጓጓዘ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
 
በተጨማሪም 1 ሺህ 222 ሜትሪክ ቶን በላይ መድሃኒት እና 7 ሺህ 651 ሜትሪክ ቶን ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች በክልሉ ለሚገኙ ተጎጂዎች ማሰራጨት መቻሉን አንስተዋል፡፡
 
ለስራ ማስኬጃ እና ለፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል 576 ሚሊየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ወደ ሽረ እና መቀሌ ከተሞች መላኩንም ተናግረዋል፡፡
 
በሌላ በኩል በትግራይ ክልል ለተለያዩ አገግልሎቶች የሚውል 690 ሺህ 868 ሊትር ባላይ ነዳጅ ወደ ክልሉ መጓጓዙን አቶ ደበበ ጠቁመዋል፡፡
 
የሰብዓዊ እርዳታዎቹ የተላኩትም በአፋር አብአላ፣ በጎንደር -ማይጠብሪ- ሽረ እንዲሁም በኮምቦልቻ-ቆቦ አላማጣ ኮሪደሮች በኩል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
አሁን ላይ 23 የሚሆኑ አጋር አካላት በትግራይ ክልል በሚከናወነው የሰብዓዊ እርታዳ ስርጭት ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.