ዓለምአቀፋዊ ዜና

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 164 ሺህ በላይ ደርሷል

By Tibebu Kebede

March 31, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 164 ሺህ 610 ደርሷል።

ከአራት ወራት በፊት በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አሁን ላይ ከ190 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ተስፋፍቷል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጅ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 787ሺህ 10 መድረሱን ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

ከዚህ ውስጥም አሜሪካ 164 ሺህ 610 በላይ የሚሆኑ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ ቀዳሚ ሆናለች።

በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 37ሺህ 829 መድረሱ ተገልጿል።

ከዚህ ውስጥም በጣሊያን 11ሺህ 591 ፣በስፔን 7ሺህ 716፣ በቻይና 3 ሺህ 187፣ በፈረንሳይ 3 ሺህ 24፣ በአሜሪካ 3 ሺህ እንዲሁም  በኢራን 2 ሺህ 757  የሚሆኑ ዜጎች  በቫይረሱ  ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል።

ይህን ተከትሎም ሀገራት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የተለያዩ እርምጃዎችን በመውስድ ላይ መሆናቸውን መጃዎች ያሳያሉ።

ምንጭ፦ሲ ኤን ኤን እና ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ