Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ድርጅቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት ለተቋቋመው ኮሚቴ ከ47 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ መንግስት ላደረገው ተድጋፍ ጥሪ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ለተቋቋመው ኮሚቴ ድጋፍ እያደረጉ ነው።

በዛሬው እለትም ወደ 12 የሚጠጉ የግል እና የመንግስት ተቋማት ከ47 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውም ተገልጿል።

በዚሁ መሰረት፦

ሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ 10 ሚሊየን 845 ሺህ ብር

ዳሽን ባንክ 10 ሚሊየን ብር

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን 10 ሚሊየን ብር

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ 5 ሚሊየን ብር

አዋሽ ኢንሹራንስ 3 ሚሊየን ብር

ዓባይ ባንክ 3 ሚሊየን ብር

ደቡብ ግሎባል ባንክ 2 ሚሊየን ብር

ሆራ ትሬዲንድ 1 ሚሊየን ብር

ትራኮን ትሬዲንግ 1 ሚሊየን ብር

ሳንታማሪታ 1 ሚሊየን ብር

ኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት 200 ሺህ ብር

ቲ ኬ ፒ.ኤል.ሲ 50 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

በዚሁ የድጋፍ ማሰባሰብ መርሃ ግብር በጥሬ ገንዝብ እና በቁሳቁሶች የሚደረጉ ድጋፎች
ተጠነባክረው መቀጠላቸውን የብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ንፁስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ተናግረዋል።

የተጀመረው የድጋፍ እንቅስቃሴ የኮሮና ቫይረስን በመከላከል ሂደትን የሚያግዝ ሲሆን፥ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በግል ከሚያደርገው ጥንቃቄ በተጨማሪ በእንበደዚህ አይነት ጥሪዎች ድጋፍ በማድረግ ምላሽ እንሰጥም ጠይቀዋል።

በዛሬው እለት ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን የዛሬወ መጀመሪያቸው መሆኑን በመግለፅ፤ በቀጣይም ድጋፍ በሚያስፈልግበት ሁሉ አስፈላጉውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

በሀይለኢየሱስ ስዩም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.