የሀገር ውስጥ ዜና

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ሊሰጥ ነው

By Amele Demsew

December 13, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገርአቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በጤና ሚኒስቴር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዮርዳኖስ አለባቸው እንደገለጹት፥ ኩፍኝን ጨምሮ የኮቪድ 19 ክትባት ይሰጣል።

ከዚህ ባለፈም የእግር መቆልመም ችግር ያለባቸውን እና የአጣዳፊ የምግብ እጥረት ልየታ እንደሚከናወንም ነው የተናገሩት፡፡

በእስካሁኑ ሂደት ከ43 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በመደበኛና በዘመቻ የኮሮና መከላከያ ክትባት መውሰዳቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ክትባቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚጀምርበትን ቀን ሚኒስቴሩ ይፋ እንደሚያደርግ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡