የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

December 13, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጃክ ሳሊቫን ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም÷በጦርነቱ ማቆም አተገባበር፣ በመንግሥት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ሥራዎች ላይ መክረዋል፡፡ እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማደስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡