
አርጀንቲና ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ አለፈች
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲና ክሮሺያን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ማለፏን አረጋግጣለች።
የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ግቦች ሊዮኔል ሜሲ እና ጁሊያን አልቫሬዝ አስቆጥረዋል።
ሊዮኔል ሜሲ የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ከፍተኛ ግብ አግቢነትን በእኩል 5 ግቦች ከፈረንሳዩ ኪሊያን ምባፔ ጋር በጋራ እየመራ ይገኛል።
ውጤቱን ተከትሎ አርጀንቲና ነገ ከሚለየው የአፍሪካዊቷ ሞሮኮ እና ፈረንሳይ አሸናፊ ቡድን ጋር ለፍጻሜ ጨዋታ የምትፋለም ይሆናል።