ዓለምአቀፋዊ ዜና

በኪንሻሳ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ከ120 በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

By Tamrat Bishaw

December 14, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ኪንሻሳ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ከ120 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ በርካቶች መቁሰላቸው ተገልጿል።

በአደጋው በኪንሻሳ ብቻ 24 መንደሮች ተጎድተዋል።

በጎርፉ ሳቢያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ መንገዶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፥ በደቡባዊ ሞንት ንጋፉላ ወረዳ በመሬት መንሸራተት ምክንያት ዋና ከተማዋን ከአትላንቲክ ውቅያኖስ የማታዲ ወደብ ጋር የሚያገናኘው ቁልፍ የአቅርቦት መስመር መቁረጡም ተነግሯል።

በዋሺንግተን በሚካሄደው የአፍሪካ – አሜሪካ ጉባኤ ላይ የተሳተፉት ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሼሲኪዲ ለሟች ቤተሰቦች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።