የሀገር ውስጥ ዜና

1ሺህ 23 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Tamrat Bishaw

December 14, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተከናወነው በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ሥራ 1ሺህ 23 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ከሕዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ 11 ሺህ 843 ኢትዮጵያውያን መመለሳቸውን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡