የሀገር ውስጥ ዜና

ሁሉም ግብሩን በወቅቱ በመክፈል ለሀገሩ እድገት አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይገባል- ወይዘሮ ዓይናለም ንጉሤ

By Shambel Mihret

December 14, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በብድርና በእርዳታ ያደገ ሀገር የለምና ሁሉም ግብሩን በወቅቱ በመክፈል ለሀገር እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት እንደሚገባ ወይዘሮ ዓይናለም ንጉሤ ገለጹ፡፡

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ግብራቸውን በታማኝነትና በወቅቱ በመክፈል ግዴታቸውን ለተወጡ 52 ግብር ከፋዮችና ተቋማት እውቅና ተሰጥቷል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ ዓይናለም ንጉሤ በእውቅና አሰጣጥ ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በብድርና በእርዳታ ያደገ ሀገር የለምና ሁሉም ግብሩን በወቅቱ በመክፈል ለሀገር እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይገባል ብለዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እንደገለጹት÷ በአስተዳደሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከናወኑ ለሚገኙ የልማት ሥራዎች የታማኝ ግብር ከፋዮች ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡

እውቅና የተሰጣቸው ግብር ከፋዮች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት አስተያየት÷ እውቅና መሰጠቱ እንዳስደስታቸው  ገልጸው በቀጣይም የሚጠበቅባቸውን  ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ