Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ህልማችን ባይሳካም ከሀዘን ይልቅ ኩራት ይሰማናል-ዋሊድ ረግራጊ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6 ፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ህልማችን ቢያበቃም ከሀዘን ይልቅ ኩራት ይሰማናል ሲሉ የሞሮኮው ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዋሊድ ረግራጊ ተናገሩ፡፡

የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ክስተት የሆነችው ሞሮኮ ሃያላን ቡድኖችን በማሸነፍ ሳትጠበቅ ግማሽ ፍጻሜ መድረስ ችላ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ በዓለም ዋንጫው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ከፈረንሳይ ጋር የተገናኘችው ሞሮኮ 2 ለ 0 ተሸንፋ የፍጻሜ ምኞቷ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የሞሮከው አሰልጣኝ ዋሊድ ረግራጊ÷ በዓለም ዋንጫው ተጋጣሚዎቻችንን ፈትነናል፤ያለንን አቅም ሁሉ ሜዳ ላይ አሳይተናል፤ይህ ለእኛ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል፡፡

ተጫዋቾቼ ምርጥ ብሄራዊ ቡድን እንዳለን ማሳያ ናቸው ያሉት አሰልጣኙ ÷አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ከፍተኛ ጉጉት ነበራቸው ሲሉ  አድንቀዋል፡፡

የዓለም ዋንጫን በተዓምር ሳይሆን ተግቶ በመስራት ብቻ ማሸነፍ እንደሚቻል ጠቁመው÷ እሳቸው እና ተጫዋቾቻቸውም ባሳዩት ድንቅ አቋም አዲስ ታሪክ ማስመዝገባቸውን አውስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.