Fana: At a Speed of Life!

2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ 21 ቀን በዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ 21ቀን 2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
 
በፈተናው የሚሳተፉትም የመጀመሪያ ዙር ፈተናን በወሊድ ወይም በእርግዝና ምክንያት ተንቀሳቅሰው መፈተን ያልቻሉ፣ በህግ ጥላ ስር ወይም በማረሚያ ቤት ሆነው በነበረው መፈተኛ ሁኔታ ለመፈተን ያልቻሉ እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ ወይም የክልል ልዩ ኃይል አባል ሆነው በወቅቱ በግዳጅ ላይ በመሆናቸው ያልተፈተኑ ተማሪዎች መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም በህመም ወይም ተቀባይነት ባገኘና ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ወይም በክፍል ፈተና ያልተፈተኑ እና በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ያልተፈተኑ ተማሪዎችን በፈተናው እንደሚሳተፉ ተጠቁሟል፡፡
 
በተጨማሪም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አንድ ፈተና እንዲፈተኑ የተወሰነላቸውና ተቀባይነት ባገኙ ችግሮች ምክንያት እንዲፈተኑ የተወሰነላቸው ተማሪዎች በፈተናው እንደሚሳተፉ የአገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ስለሆነም ተፈታኞች ይህንን ተገንዝበው አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አገልግሎቱ አሳስቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.