የሀገር ውስጥ ዜና

4 ሺህ 35 ግራም የኮኬይን እፅ ይዞ የተገኘው ናይጄሪያዊ በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ

By Mikias Ayele

December 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 4 ሺህ 35 ግራም የሚመዝን የኮኬይን እፅ ይዞ የተገኘው ናይጄሪያዊ በፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጣቱን የፍትህ ሚኒስቴር  አስታውቋል፡፡

ፒተር ኢመሀን የተባለው ናይጀሪያዊ  ከብራዚል በመነሳት በኢትዮጵያ አየር መንገድ  ወደ ናይጄሪያ ሊጓዝ ሲል በቦሌ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገ  ፍተሻ 4 ሺህ 35 ግራም የሚመዝን ኮኬይን በወገቡ ላይ በማሰር ይዞ መገኘቱ ተገልጿል፡፡እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ 12 ሺህ 857 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም ግለሰቡ በፈፀመው አደገኛ እፆችን የማዘዋወር ወንጀል ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶበታል፡፡

ተከሳሹም ክሱ ተነቦለት የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሜያለሁ ያለ ሲሆን÷ ዐቃቤ ሕግም ተከሳሹ የተከሰሰበትን የወንጀል ድርጊት ሙሉ በሙሉ ያመነ በመሆኑ በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ይሰጥልኝ ሲል ጠይቋል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተውም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ችሎትም ተከሳሹ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ20 ሺህ ብር እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡