Fana: At a Speed of Life!

ሙስናን በተቀናጀ መንገድ በመከላከል የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት ይሰራል – የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሙስናን በተቀናጀ መንገድ በመከላከል የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እንዳሉት የሙስናና የሌብነት ተግባራትን በተቀናጀ መንገድ በመከላከል የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ሥራ የህዝብን መሠረታዊ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የመመለስ ጉዳይ ነው፡፡

ከንቲባው አምስት ተቋማትን ያካተተ የፀረ ሙስና ኮሚቴ እና ኮሚሽን ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ጠቁመዋል።

ኮሚቴው በአስተዳደሩ የፍትኅ ፀጥታና የኅግ ጉዳዮች ቢሮ የሚመራ ሲሆን የፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የአስተዳደሩ ኦዲት ፅኅፈት ቤት፣ የፌዴራል ዐቃቢ ኅግ እንዲሁም የከንቲባ ፅኅፈት ቤት ቅሬታ ሰሚ የተካተቱበት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ኮሚቴው በአስተዳደሩ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ በሚገኘው የሙስና ተግባራት እና ለሌብነት የሚያጋልጡ አሠራሮችን በመፈተሽ መሠረታዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አስታውቀዋል።

ኅብረተሰቡ ከኮሚቴው እና ከኮሚሽኑ ጋር በቅርበት በመስራት የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ለመመለስ እና የኅግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ማሳካት አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.