የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል ከ700 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ተሸፈነ

By Meseret Awoke

December 17, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮ ዓመት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ለመሸፈን ከታቀደው 1 ሚሊየን ሄክታር እስካሁን 700 ሺህ ሄክታር በዘር መሸፈን መቻሉን ተገለፀ ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ መሃመድ ሳኒ÷ በክልሉ 21 ዞኖችና 19 ከተሞች በተከናወነ የንቅናቄ ስራ ይህ ውጤት እውን ሆኗል ብለዋል፡፡

የጅማ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ቱጃኒ ናስር በበኩላቸው፥ የስንዴ ልማት ስራው እንደ ሀገር በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ለውጭ ገበያ የማቅረብ ትልማችን እውን እንዲሆን በትኩረት መስራታችን ውጤታማ አድርጎናል ብለዋል።

ለዚህም በየደረጃው ያሉ የግብርና ባለሙያዎችንና አመራሮች እንዲሁም አርሶ አደሩን አመስግነዋል።

በቡና ምርት የምትታወቀው የጅማ ዞን ጎማ ወረዳ አርሶ አደሮችም፥ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በክላስተር የጀመርነው የስንዴ ልማት በዓመት ሁለት ጊዜ እንድናመርት እድል ስለከፈተልን የተሻለ ገቢ ተጠቃሚ ሆነናል ብለዋል።

በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ በዘርፉ የተከናወኑ ስራዎችና የህብረት ስራ ማህበራት የመስክ ምልከታ ተደርጎባቸዋል።

በጎህ ንጉሱ