ስፓርት

ክሮሽያ በአለም ዋንጫ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

By Shambel Mihret

December 17, 2022

በአዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር የዓለም ዋንጫ ክሮሽያ ሞሮኮን 2 ለ 1 በማሸነፍ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

ጨዋታው ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ የተደረገ ሲሆን÷በ2022ቱ የዓለም ዋንጫ ሞሮኮ ከክሮሽያ ጋር ያደረገችው ጨዋታ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ 3ኛ ሆኖ የሚያጠናቅቀው ብሔራዊ ቡድን የተለየበት ነው፡፡

ሞሮኮ 3ኛ ደረጃን ይዛ የማጠናቀቅ ሕልሟ ባይሳካም ከዓለም 4ኛ በመሆን ታሪክ የሠራች ቀዳሚዋ የአፍሪካ ሀገር መሆን ችላለች።

ሞሮኮ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለግማሽ ፍፃሜ የደረሰች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር የሆነችበት ጉዞ በፈረንሳይ 2 ለ 0 አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል።