Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ልዑክ በደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፈ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ልዑካን ቡድን አባላት በደቡብ አፍሪካው ገዢ ፓርቲ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ 55ኛ ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

ብልጽግና ፓርቲ እና የደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ዘላቂ የሆነ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ትስስር ይበልጥ ሊያጠናክር የሚችል ግንኙነት በመመስረት ላይ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ከፓርቲው የቀረበለትን ጥሪ በመቀበል ታሪካዊ የሆነውን ግንኙነት ለማጠናከር በ55ኛው የፓርቲው ኮንፍረንስ ላይ እንዲሳተፉ ተወካዮቹን መላኩ ነው የተገለጸው፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ተወካዮችም የአጋርነት እና በቅንጅት ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት በኮንፍረንሱ ላይ መግለጻቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ልዑካኑ ከፓርቲው ኮንፍረንስ ተሳታፊነት በተጨማሪ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር መወያየታቸው ተጠቁሟል፡፡

በዚህ ወቅትም ደቡብ አፍሪካ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ለመፍታት ላበረከተችው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

በፕሪቶሪያ የተፈረመውን ስምምነት ለመፈጸም ብልጽግና ፓርቲ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ልዑካኑ ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.