Fana: At a Speed of Life!

በተቋማት የሚገኙ ቁርጥራጭ ብረቶችና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ተሽከርካሪዎች የመሸጫ ዋጋ ማሻሻያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግሥት ተቋማት የሚገኙ ቁርጥራጭ ብረቶችና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ተሽከርካሪዎች የመሸጫ ዋጋ ማሻሻያ መደረጉን የማዕድን ሚኒስቴር እና የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን ዛሬ ይፋ አድርገዋል፡፡

የማዕድን ሚኒስቴር በቁርጥራጭ ብረታ ብረት እና ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የዋጋ ማሻሻያ ዙሪያ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

ባለፉት ጊዚያት የወጣው የዋጋ ተመን ቁርጥራጭ ብረት የማዘጋጃ የመጫኛ፣ የማውረጃ እና የማጓጓዣ ወጪ ግምት ውስጥ ያስገባ ባለመሆኑ የዋጋ ማሻሻያ እንዲደረግ መወሰኑ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረት ስቲል 64 ብር የነበረው 48 ብር በኪሎ ግራም ሲሆን ካስት አይረን 51 ነጥብ 75 ብር በኪሎ ግራም የነበረው 35 ብር እንዲሸጥ ተወስኗል።

እንዲሁም ስክራፕ ያደረገ ተሽከርካሪ ወይም ማሽነሪ እና ያገለገሉ የተሽከርካሪ ማሽነሪ መለዋወጫ 51 ነጥብ 25 ብር የነበረው 39 ብር በኪሎ ግራም እንዲሁም 120 ብር የነበረው አሉሙኒየም 90 ብር በኪሎ ግራም እንዲሸጥ ተወስኗል።

አምራች ኢንዱስትሪውን ለማበረታታት የማዘጋጃ፣ የመጫኛ እና የማጓጓዣ ወጪዎችን እንደ ክብደቱ መጠን እና የቦታ ርቀቱን ታሳቢ ያደረገ የዋጋ ቅናሽ ይደረጋል ተብሏል።

በፌዴራል መንግስት ተቋማት በክልሎች እና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ቁርጥራጭ ብረቶች ለብረት አምራች ፋብሪካዎች በቀጥታ ሽያጭ እንዲተላለፉ በመስከረም ወር አጋማሽ ይፋ በማድረግ ወደስራ መገባቱ ይታወሳል፡፡

በምንይችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.