በፕሪሚየር ሊጉ መቻል ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል ባህርዳር ከነማን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በድሬዳዋ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ መቻል ከመመራት ተነስቶ በሃሉ ግርማ፣ በረከት ደስታ እና ከነዓን ማርክነህ ባስቆጠሯቸው ግቦችአሸናፊ መሆን ችሏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ የጣና ሞገዶቹ ፕሪሚየር ሊጉን የሚመሩበትን እድል ሲያመክኑ÷ መቻል በአንፃሩ አራት ደረጃዎችን በማሻሻል ከወልቂጤ ከነማ ጋር እኩል 7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡
የ13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በድሬዳዋ ስታዲየም መካሄዳቸው ሲቀጥል ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሀድያ ሆሳዕና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡