የሀገር ውስጥ ዜና

የአረንጓዴ አሻራ እንክብካቤ ዘመቻ በኦሮሚያ ክልል ተጀመረ

By Shambel Mihret

December 20, 2022

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ አሻራ እንክብካቤ ዘመቻ በኦሮሚያ ክልል ተጀምሯል፡፡

በሀገሪቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እንደ ሀገር ከተተከሉት 25 ቢሊዮን ችግኞች 13 ነጥብ 6 ቢሊየን ችግኞች በኦሮሚያ እንደተተከሉ ተገልጿል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ እንክብካቤ ዘመቻው በምስራቅ ባሌ ዞን ግንዲር ከተማ እና በጅማ ዞን ሰቃ ጮቆርሳ ወረዳ መጀመሩን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡