Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ጥር 29 ቀን ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ሕዝበ ውሳኔ እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡

ቦርዱ ለዚሁ ዓላማ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በተጠቀሱት ቦታዎች ዛሬ ታኅሣሥ 11 ቀን 2015 ዓ.ም የመራጮች ምዝገባ መጀመሩን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በክልሉ ሕዝበ ውሳኔው የሚካሄድባቸው ስድስት ዞኖች ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ እና ጎፋ ሲሆኑ÷ አምስቱ ልዩ ወረዳዎች ደግሞ ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ እና ደራሼ ናቸው።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.