ጠ/ሚ ዐቢይ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጋር በኮሮ ናቫይረስ ዙሪያ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ በስልክ ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ እንደሳፈሩት፥ የኮቪድ 19ን ተጽዕኖ በአብሮነት ለማሸነፍ እንዲቻል የጋራ አመራር እንደሚያስፈልግ በውይይታቸው ላይ አንስተዋል።
ወረርሽኙ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል የቡድን 20 ሀገራት፣ የዓለም ባንክ እንዲሁም የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም /አይ ኤም ኤፍ/ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ መስማማታቸውንም ነው የገለፁት።
ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር መሆናቸው ይታወቃል።