የሀገር ውስጥ ዜና

ሁለት ላብሪቶሪዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጀመሩ

By Tibebu Kebede

April 01, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአርማዎር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዮት እና በብሄራዊ የእንስሳት ጤና ምርመራና ጥናት ማዕከል የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተጀመረ።

ሁለቱ ተቋማት 4 አርቲ ፒ ሲ አር ማሽኖችን በመጠቀም በቀን ውስጥ እስከ 400 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንደሚያደርጉ ነው የተነገረው።

ለዚህም የሚያስፈልጉ 4 አርቲ ፒ ሲ አር ማሽኖች በተቋማቱ ሁለት ሁለት እንደሚገኙ ተነግሯል።

ለቤተ ሙከራ ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ ስልጠናዎችን ጨምሮ የምርመራ ቁሳቁሶች እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶች መቅረባቸውን የኢትዮጵያ የማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ቶሌራ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ሂደትም በብሄራዊ የቤተ ሙከራ አቅም ግንባታ አስተባባሪነት የሚካሄድ ነው ተብሏል