የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ መግቢያ በሮች 4 ግዙፍ የግብርና ምርቶች ማከፋፈያ የገበያ ማዕከላት እየተገነቡ ነው

By Meseret Awoke

December 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የመግቢያ በሮች ላይ አራት ግዙፍ ሁለገብ የግብርና ምርቶች ማከፋፈያ የገበያ ማዕከላት እየተገነቡ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው እንዳሉት ፥ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሁለት፣ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አንድ እንዲሁም በንፋስ ሥልክ ላፍቶ ክፍለከተማ አንድ በድምሩ አራት ግዙፍ የግንባታ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ነው፡፡

የገበያ ማዕከላቱ ከፍተኛ የግብርና ምርትን በመያዝ፣ የኑሮ ውድነቱን ጫና በመቀነስ፣ ገበያን በማረጋጋትና በመቆጣጠር የራሳቸውን ሚና የሚጫወቱ ናቸው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ለተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሥራ ዕድልን እንደሚፈጥሩም ነው የገለጹት፡፡

ግንባታቸውም በታለመለት ጊዜና ወጪ እንዲጠናቀቅ የጀመርነውን የቅርብ ክትትልና ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለንም ብለዋል ከንቲባዋ፡፡